እንኳን ወደ ጋዜጠኞች ደህንነት ፖርታል መጡ
የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ደህንነትን የተመለከቱ ጉዳዮች የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር (ኢአማ) አንዱ እና ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ማህበራችን በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ባሻገር የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የመገንባት ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ ያምናል፡፡እንደ ግድያ ፣ እስር ፣ ግዞት ፣ ከበርካታ አካላት የሚሰነዘሩ ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች ፣ የጋዜጠኞችን እና የቤተሰባቸውን ስብዕና የሚያጎድፉ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች እና ሌሎች ተዛማች ጥቃቶች በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ታሪክ ውስጥ አብረው የሚነሱ እና የኖሩ ክስተቶች ናቸው፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
ኢአማ ከ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሱ የጥቃት ክስተቶችን በመሰብሰብ ፣ በማጣራት እና ይፋ በማድረግ መፍትሔ እንዲገኝ የሚያስችል አሰራር ጀምሯል፡፡ ይህንንም መረጃ ግብአት በማድረግ በየአመቱ መጨረሻም የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ደህንነት ደረጃ ሪፖርት አውጥቶ ያሳትማል፡፡
በዚህ ድህረ-ገፅ አማካኝነት የሚሰበሰቡት እነዚህ የጥቃት ክስተቶች በዋናነት በመላው ኢትዮጵያ ባሉ አባሎቻችን አስተባባሪነት እንዲሁም በዜጎች እና ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ የሚደረጉ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ነው፡፡
ሴት ጋዜጠኞች በስራ ቦታቸውም ሆነ በጋዜጠኝነት ጉዞአቸው ላይ የሚደርሱባቸው ፆታዊ ጥቃቶች እንደ ዋና ክስተት የሚጠቆም ሲሆን ፣ ኢአማ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ የመፍትሄ ሒደቶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፡፡
የእርስዎ ድጋፍ የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር (ኢአማ) በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ከመከላከል ባሻገር የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የመገንባት ሂደት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
‐‐
የአካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃት ጥቆማዎች
በሴት ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ዛቻ
‐‐
በሴት ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት
በእስር ላይ ተከሰው ያሉ ጋዜጠኞች
‐‐
በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች